ስለHuawei HiSuite እና ግላዊነት መግለጫ
Huawei HiSuite በ Huawei Device Co., Ltd. እና በስሩ ያሉ አለምአቀፍ ድርጅቶች (ከዚህ በኋላ "Huawei" "እኛ"፣ ወይም "የእኛ" ተብሎ የሚጠራ) የሚከወን የውሂብ መጠባበቂያ እና መልሶ ማግኘት፣ የስርዓት ዝማኔ እና ለሞባይል መሳሪያዎችዎ ደረጃን ማሳደግን የሚያቀርብ ምርት (ወይም አገልግሎት) ነው። የግል መረጃዎ ያለውን አስፈላጊነት እንረዳለን፣ እናም ለመጠበቅ የአቅማችንን ሁሉ እናደርጋለን። በኢንዱስትሪያዊ ደህንነት ደረጃ መሰረት ግላዊ መረጃዎን ለመጠበቅ አግባብ የሆኑ የደህንነት እርምጃዎችን እንደምንወስድ ቃል እንገባለን።
ይህንን ምርት (ወይም አገልግሎት) ከመጠቀምዎ በፊት እባክዎ ስለHuawei HiSuite እና ግላዊነት መግለጫ ያንብቡና ይረዱት።
ይህን ምርት (ወይም አገልግሎት) መጠቀም ሲጀምሩ አዋቂ እንደሆኑ እያረጋገጡና ዋስትና እየሰጡ ነው። ለአካለ መጠን ካልደረሱ አሳዳጊዎ ይህንን ምርት (ወይም አገልግሎት) እንዲጠቀሙ መስማማትና እንዲሁም ከተዛማጅ የመተግበሪያው ደንቦች ጋር መስማማት ይኖርባቸዋል።
ማናቸውም ጥያቄዎች፣ አስተያየቶች ወይም ሀሳብ ካለዎት እባክዎ በደንበኛ አገልግሎት መስመር፦ 400-830-8300/800-830-8300፣ በመስመር ላይ የደንበኛዎች አገልግሎት በኩል ወይም በዓለምአቀፍ ቢሮዎቻችን ላይ ያነጋግሩን። ለተሟላ የቢሮዎቻችን ዝርዝር እባክዎ የHuaweiን ያነጋግሩ ገጽ ይጎብኙ።
የግላዊነት ጥያቄዎች ገጹን በመጎብኘት ሊያገኙት የሚችሉት ለግል መረጃ ጥበቃ የተመደበ መምሪያ (ወይም ልዩ ባለሙያዎች) መምሪያ አለን።
በመደበኛ ሁኔታዎች ላይ በወር ውስጥ ምላሽ እንሰጠዎታለን።
በምላሻችን ካልተደሰቱ፣ በተለይ የግል መረጃዎ አካሄዳችን ወይም አያያዛችን ህጋዊ መብቶችዎን እና/ወይም ጥቅሞችዎን እንደሚጥስ ወይም እንደሚጎዳ ካመኑ፣ በሚመለከተው የህግ ክልል ውስጥ ላለው የሕዝብ ፍርድ ቤት መክሰስ ሆነ በሚመለከታቸው የኢንዱስትሪ ማህበር ወይም የመንግስት ተቆጣጣሪ ወኪሎች ጋር ቅሬታ ማስገባት ውጫዊ መፍትሔ መፈለግ ይችላሉ።
1. የእርስዎን የግል መረጃ እንዴት እንደምንሰበስብ እና እንደምንጠቀም
የግል መረጃ ማለት አንድ የተወሰነ ተፈጥሯዊ ሰውን ለመለየት ወይም የአንድ የተወሰነ ተፈጥሯዊ ሰው እንቅስቃሴን ለማንጸባረቅ ለብቻው ወይም ከሌላ መረጃ ጋር መጠቀም የሚቻል በኤሌክትሮኒካዊ ወይም ሌላ መንገድ የተመዘገበ የተለያየ መረጃ ነው።
ሚስጥራዊነት ያለው የግል መረጃ የግል መለያ ቁጥርን፣ የግል ባዮሜትሪክ መረጃን፣ የባንክ ሒሳብ ቁጥርን፣ የንብረት መረጃን፣ የት እንዳሉ፣ የግብይት መረጃን፣ እና 14 ዓመት እና ከዚያ በታች የሆኑ የልጆች የግል መረጃን ያካትታል።
የግል መረጃዎን የምንሰበስበውና የምንጠቀመው በዚህ መግለጫ ውስጥ ለተጠቀሱት ለሚከተሉት ዓላማዎች ብቻ ነው፦
የሚከተሉትን ወሳኝ ተግባሮች ለእርስዎ ማቅረብ
(1) መጠባበቂያ እና መልሶ ማግኛ
የመጠባበቂያ እና መልሶ ማግኛ አገልግሎቶቹን ለእርስዎ ለማቅረብ የሚከተለውን መረጃዎን መሰብሰብ አለብን፦
የመሳሪያ መለያ፣ ስርዓተ ክወና፣ የመሳሪያ ስም፣ የመሳሪያ ሞዴል፣ የመሳሪያ IP እና የመሳሪያ ሃርድዌር መረጃ (እንደ የሲፒዩ ሞዴል እና የሮም/ራም መረጃ ያለ) ጨምሮ የመሳሪያ መረጃ።
የHiSuite ስሪት እና የስርዓተ ክወና ስሪት ጨምሮ የኮምፒውተር ሶፍትዌር መረጃ።
ቀዳሚው ውሂብዎ በመሳሪያዎ ላይ ብቻ ነው የሚከማቸው፣ እና ወደ የHuawei አገልጋዮች አይሰቀልም።
(2) የሞባይል ስልክ ስርዓት ዝማኔ እና ጥገና
ወዲያውኑ የስርዓት ዝማኔ እና የጥገና አገልግሎቶችን ለእርስዎ ለማቅረብ የሚከተለውን መረጃዎ መሰብሰብ አለብን፦
የመሳሪያ መለያ፣ የመሳሪያ ስም፣ የመሳሪያ ሞዴል፣ የመሳሪያ ሲፒዩ ሞዴል፣ የሮም/ራም መረጃ እና የስርዓት ስሪት ጨምሮ የመሳሪያ መረጃ።
የእርስዎ IP አድራሻ ጨምሮ የኮምፒውተር አውታረ መረብ መረጃ።
እንዲህ ያለ የመረጃ መሰብሰብ ዓላማው ከመሳሪያዎ ጋር የሚዛመድ የሮም ስሪት ለማቅረብ ነው።
የእርስዎን የግል መረጃ በሚከተሉት መንገዶች እንጠቀምበታለን፦ እርስዎ በሚያቀርቡት የመሳሪያ እና የስርዓት መረጃ ላይ በመመስረት ለመሳሪያዎ አግባብ የሆነውን የሮም ስሪት ማግኘትና መግፋት፣ እንዲሁም በስርዓቱ ውስጥ ሊኖሩ የሚችሉ ስጋቶችን ለመፍታት የእርስዎን ፈቀዳ ካገኘን በኋላ የቅርብ ጊዜውን ሮም ማውረድና ስርዓትዎን ማዘመን።
እንዲህ ያለውን መረጃን የማይሰጡ ከሆነ ስርዓትዎን ማዘመን እና ነባሮቹን የደህንነት ስጋቶች መጠገን አንችልም።
(3) የመተግበሪያ ዝማኔዎች እና ውርዶች
በስርዓትዎ ላይ ለተጫኑ መተግበሪያዎች ዝማኔዎችን እና ውርዶችን ለመተግበር የሚከተሉትን መረጃዎችዎ መሰብሰብ አለብን፦
የመተግበሪያ ስም እና ስሪት ጨምሮ የመተግበሪያ መረጃ።
የመሳሪያ መለያን እና UDID ጨምሮ የመሳሪያ መረጃ።
የእርስዎ IP አድራሻ እና የማክ አድራሻ ጨምሮ የኮምፒውተር አውታረ መረብ መረጃ።
እንዲህ ያለ የመረጃ መሰብሰብ ዓላማው ከመሳሪያዎ ጋር የሚዛመድ የመተግበሪያ ስሪትን ለማቅረብ ነው።
የእርስዎን የግል መረጃ በሚከተሉት መንገዶች እንጠቀምበታለን፦ እርስዎ በሚያቀርቡት የመተግበሪያ፣ የመሳሪያ እና የስርዓት መረጃ ላይ በመመስረት አግባብ የሆነውን የመተግበሪያ ስሪት ማግኘት እና መግፋት፣ እና የእርስዎን ፈቀዳ ካገኘን በኋላ የመተግበሪያው የቅርብ ጊዜውን ስሪት ማውረድ።
እንዲህ ያለውን መረጃን የማይሰጡ ከሆነ የመተግበሪያው የቅርብ ጊዜውን ስሪት ማግኘት፣ ማዘመን እና ማውረድ አንችልም።
(4) አገልግሎትን ማሻሻል
የተሻለ የአገልግሎት ተሞክሮን ለእርስዎ ለማቅረብ የሚከተለው መረጃዎን መሰብሰብ አለብን፦ የመተግበሪያ ስታቲስቲክስ እና የHiSuite አጠቃቀም ባህሪ ውሂብ። እንዲህ ያለ የመረጃ መሰብሰብ ዓላማው ከመሳሪያዎ ጋር የሚዛመድ የመተግበሪያ ስሪትን ለማቅረብ ነው።
የእርስዎን የግል መረጃ በሚከተሉት መንገዶች እንጠቀምበታለን፦ በእርስዎ የመተግበሪያ ስታቲስቲክስ እና የHiSuite አጠቃቀም ባህሪ ውሂብ ላይ በመመስረት የተሻለ የተጠቃሚ ተሞክሮን እና ግላዊነት የተልአበሱ ምርቶችንና አገልግሎቶችን ለእርስዎ ማቅረብ።
ይህን ባህሪ መጠቀም ለመጀመር ወይም ለማቆም በHiSuite ውስጥ ወደ ቅንብሮች > አጠቃላይ በመሄድ በቀላሉ የተጠቃሚ ተሞክሮ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ምልክት ያድርጉ ወይም ምልክቱን ያንሱት።
2. የእርስዎ ውሂብ ጉዳይ መብቶች
በሚመለከታቸው ህጎች መሠረት በውሂብ ጉዳይ መብቶች ይደሰታሉ። ስለውሂብ ጉዳይ መብቶችዎ ማናቸውም ጥያቄዎች፣ አስተያየቶች ወይም ጥቆማዎች ካለዎት እባክዎ በዚህ መግለጫ ውስጥ ያለውን የእውቂያ መረጃ ተጠቅመው ያነጋግሩን።
3. የውሂብ ማከማቻ አካባቢ እና ጊዜ
(1) የውሂብ ማከማቻ ቦታ
በሞባይል ስልክ ስርዓት ዝማኔው እና የጥገና አገልግሎቶች ስር የምንሰበስበውና የምናመነጨው የግል መረጃ በሕዝባዊ ቻይና ሪፐብሊክ ውስጥ በሚገኙ አገልጋዮች ላይ ይከማቻሉ
(2) የውሂብ ማከማቻ ጊዜ
የእርስዎን የግል መረጃ የምናከማቸው ለዓላማዎቹ ለሚያስፈልግበት ጊዜ ብቻ ሲሆን በሚመለከታቸው ህጎች እና ደንቦች ካልተጠየቀ በስተቀር ከታች የተመለከተው የጊዜ ገደብ ሲያልፍ የእርስዎን የግል መረጃ እንሰርዛለ ወይም ማንነት እንዳይገልጽ እናደርገዋለን።
ለሞባይል ስልክ ስርዓት ዝማኔዎች እና የጥገና አገልግሎቶች የግል ውሂብዎ ትክክለኛው የማቆያ ጊዜ እንደሚከተለው ነው፦
ከላይ የተገለጸው የግል ውሂብ እርስዎ ከእኛ ጋር መስተጋብር ከፈጠሩበት የመጨረሻው ቀን ከስድስት (6) ወራት በኋላ ይሰረዛል፣ በዚህ ጊዜ ምንም የንግድ ግብይቶች ካልተፈጠሩ በስተቀር።
በተጨማሪም፣ ምርቶቻችንን ወይም አገልግሎቶቻችንን ብናቋርጥ በተገፊ ማሳወቂያ፣ በመግለጫ ወይም በሌሎች መንገዶች እናሳውቀዎታለን፣ እና ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ ውስጥ የግል መረጃዎን እንሰርዘዋለን ወይ ማንነትን የማያሳውቅ እናደርገዋለን።
4. የዚህ መግለጫ ዝማኔዎች
Huawei በየትኛውም ሰአት ላይ ይህንን መግለጫ የማዘመን መብት አለው። አንድ ለውጥ ሲከሰት የለውጥ ማሳወቂያ በብቅ-ባይ መገናኛ ሳጥን መልኩ እንልክልዎታለን። በእርስዎ ፈቃድ ብቻ ነው የግል መረጃዎን በተዘመነው መግለጫ መሠረት የምንሰበስበው፣ የምንጠቀመው እና የምናከማቸው።
ይህ መግለጫ የሚተገበረው ከተዘመነበት ቀን ጀምሮ ነው።
መጨረሻ የተዘመነው፦ ኤፕሪል 25፣ 2018
አስፈላጊ፦ ይህ የግላዊነት መግለጫ የHuawei HiSuite መተግበሪያውን የግላዊነት መግለጫ እና ቁርጠኝነት ያጠቃልላል። ስለውሂብ ጉዳዮች መብቶች፣ የመረጃ ደህንነት እርምጃዎች እና ሌሎች ዝርዝሮች ተጨማሪ ለማወቅ እባክዎ የHuawei የሸማቾች ንግድ ግላዊነት መግለጫን ያንብቡ።